1. ጭንቀት፡-
በሚጨናነቁበት ወቅት ሰዉነትዎ የተፈጠረዉን ጭንቀት ለመቀነስ የደም ስኳር መጠንዎን ይጨምራል፡፡ በቀን ውስጥ ለራስዎ ለ15 ደቂቃዎች ያህል ጊዜ በመስጠት ጭንቀትዎን መቀነስ ይችላሉ፡፡ ይህም ወክ ማድረግ፣ሙዚቃን በማዳመጥ አሊያም ፊልሞችን በማየት ሊሆን ይችላል፡፡
2. የእንቅልፍ እጦት፡-
በዲያቤትክ ኬር ጆርናል ላይ በወጣዉ ጥናት መሰረት በቂ እንቅልፍ የማያገኙ ሰዎች የሰዉነት ሴሎቻቸዉ የስኳርን መጠን ለሚቀንሰዉ ሆርሞን/ኢንሱሊን ስለማይታዘዙ/ሬዚስታንስ ስለሚፈጥሩ ለደም ስኳር መጠን መጨመር ምክንያት ይሆናል፡፡
3. የወር አበባ ዑደት፡-
ብዙዎቹ የስኳር ህመም ያለባቸዉ ሴቶች በወር አበባ ዑደታቸዉ ወቅት የሆርሞን መጠን መዛባት ስለሚያጋጥማቸዉ የደም የስኳር መጠናቸዉ ይጨምራል፡፡በወር አበባ ዑደትዎ ወቅት የኢስትሮጂንና ፕሮጀስትሮን ሆርሞን መጠን መጨመርና መቀነስ ስለሚታይባቸዉ የኢንሱሊን ሆርሞን እንዳይሰራ/ሬዚስታንስ እንዲፈጠር ያደርጋሉ፡፡
4. የፈሳሽ እጥረት፡-
የስኳር ህመምተኛ ከሆኑ በቀን ዉስጥ በቂ ፈሳሽ መዉሰድ ይጠበቅብዎታል፡፡ ምክንያቱም ሰዉነትዎ ፈሳሽ ሲያጥረዉ በደም ዉስጥ ያለዉ የስኳር መጠን ሲለሚያይል የስኳር መጠኑ ይጨምራልና፡፡