ዚካ ቫይረስ

zikra

ዚካ ቫይረስ በወባ ትንኝ የሚተላለፍ የቫይረስ አይነት ነዉ፡፡ ብዙዎቹ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ምንም የህመሙ ምልክት ባያሳዩም ጥቂት በሆኑ ሰዎች ላይ ህመሙ ትኩሳት፣የቆዳ ላይ ሽፍታና የጡንቻ ላይ ህመም ይታይባቸዋል፡፡ ሌሎቹ የህመም ምልክቶች ደግሞ የራስ ምታት፣የአይን መቅላት (ኮንጀክትቫይትስ) ና በአጠቃላይ ሰዉነት ላይ የጤነኝነት ስሜት ያለመሰማት ናቸዉ፡፡ የዚካ ቫይረስ የህመም ምልክቶች በዚካ ቫይረስ በተያዘች የወባ ትንኝ በተነከሱ ከሁለት እስከ ሰባት ቀናት ባሉት ጊዜያት ዉስጥ መታየት ይጀምራል፡፡


እናቶች በዚካ ቫይረስ በእርግዝናቸዉ ወቅት ከተያዙ የሚወለደዉ ህፃን የጭንቅላት መጠን መቀነስ (Microcephaly) የሚባለዉን ችግር እንዲታይ ከማድረጉም በላይ ለህልፈተ ህይወት ሊያደርስ ይችላል፡፡ በተጨማሪም ጉሊያንባሬ ሲንድረም የሚባለዉን የነርቭ ችግርም ሊያመጣ ይችላል፡፡
እስከ አሁን ይህን ቫይረስ ለመከላከል የሚረዳ ክትባትማ ሆነ ከቫይሱ ሊያድን የሚችል ህክምና የለም፡፡

 

ዚካ ቫይረስ የት ይገኛል፡-

 

ዚካ ቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ እ.ኤ.አ በ1947 በአፍሪካ ዉስጥ ዚካ ሸለቆ ዉስጥ የተገኘ ሲሆን ከዚያን በኃላ ደቡብና በደቡብ ምስራቅ ኢስያ፣ የፓስፊክ ደሴቶችና በአሜሪካ ታይል፡፡ እ.ኤ.አ ከግንቦት 2015 ጀምሮ በብራዚል 650 ሰዎች መታመማቸዉን ተገልፃል፡፡

 

የመተላለፊያ መንገዶች፡-

 

የዚካ ቫይረስ ኤዲስ በሚባሉ የወባ ትንኝ ዘሮች የሚተከላለፍ ሲሆን ትንኟ በመላ አለም ተሰራጭታ ትገኛለች፡፡ የዚካ ቫይረስ ከሰዉ ወደ ሰዉ አይተላለፍም፡፡

 

መከላከል፡-

 

የወባ ትንኝና የመራቢያ ቦታዋ ለዚካ ቫይረስ መዛመት ትልቁን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡ ስለሆነም መከላከልና ቁጥጥሩ የሚመሰረተዉ የወባ ትንኝ ቁጥራቸዉን ከመራቢያ ቦታቸዉ በመቀነስ ( የመራቢያ ቦታቸዉን በማጥፋት) ና የሰዉንና የትንኛን ግንኙነት መቀነስ ናቸዉ፡፡
ይህን ለማድረግ ሰዉነት ክፍሎቻችንን የሚሸፍኑ አልባሳትን በመልበስ፣ ትንኞቹን ሊያባርሩ የሚችሉ ቅባቶችን በመቀባት(insect repellent)፣ የወባ ትንኝ መከላከያ አጎበር መጠቀምና በርና መስኮትን መዝጋት ናቸዉ፡፡ በተጨማሪም ማንኛዉንም ዉሃ ሊያቁር የሚችሉ ነገሮችን/ቦታዎችን ማጥፋት ወይም መሸፈን ያስፈልጋል፡፡
ተጓዦች ራሳቸዉን ከወባ መነደፍ ለመከላከል ከላይ የተጠቀሱትን ቅድመ ጥንቃቄ ምክሮች በመትገበር እራሳቸዉን መጠበቅ ይገባቸዋል፡፡

Recent Posts

Archives

Comments

comments