ኦቲዝም

 

ኦቲዝም በህፃናት ላይ የነርቭና የእድገት ክትትል ላይ ከፍተኛ ችግር የሚፈጥር ሲሆን የልጁን ከሰዉ ጋር የሚያደርገዉን ግንኙነትና የመግባባት ችሎታ/ክህሎት  የሚጎዳ/የሚቀንስ የህመም አይነት ነዉ፡፡

የህመሙ ምልክቶች

ኦቲዝም  የልጆን ከሌሎች ጋር መግባባትንና የአረዳድ ሁኔታን በመጉዳት ለእድገት አስፈላጊ የሆኑ እንደ ማህበራዊ ግንኙነቶች፣መግባባትና ባህሪያቶችን ሊጎዳ ይችላል፡፡

የኦቲዝም ምልክቶችን አንዳንዴ በጨቅላ ህፃናት ላይ ሊታይ ይችላል፡፡ሎሎች ህፃናት ደግሞ የመጀመሪያ ወራት ወይም አመታት ላይ ያለምንም ችግር ያድጉና ድንገት መነጠል ወይም ሃይለኛ መሆን አሊያም በቅርቡ ደርሰዉበት የነበረዉን የsንs ክኅሎት እድገት በድንገት መቀነስ ይታይባቸዋል፡፡

ለችግሩ መከሰት የሚያጋልጡ ነገሮች

·         የልጅዎ ፆታ፡- ከሴቶች ይልቅ ወንዶች እስከ አራት ጊዜ እጥፍ ተጋላጭ ናቸዉ፡፡

·         በቤተሰብ ዉስጥ መሰል ችግር ከነበረ፡- በቤተሰብ ዉስጥ መሰል ችግር ያለበት ልጅ ያላቸዉ ቤተሰቦች ቀጣይ የሚወልዷቸዉ ልጆች ላይ የመከሰት እድሉ ከፍተኛ ነዉ፡፡

·         ያለቀናቸዉ በሚወለዱ ህፃናት ላይ፡- የመዉለጃ ጊዜያቸዉ ሳይደርስ ከ26 ሳምንታትና ከዚያ በታች የሚወለዱ ህፃናት ላይ የመከሰት እድሉ ከፍተኛ ነዉ፡

·         የወላጆች እድሜ፡- ተጨማሪ ጥናቶች የሚያስፈልግ ቢሆንም እድሜቸዉ ከገፉ ወላጆች የሚወለዱ ህፃናት ከሌሎች አንፃር ችግሩ ሊከሰትባቸዉ ይችላል፡፡

ህክምና

ኦቲዝምን ሊያድን የሚችል ምንም አይነት ህክምና እስከአሁን የለም፡፡ ስለሆነም የህክምናዉ ዋና አላማ ልጅዎ ላይ የሚታዩትን የህመም ምልክቶች በመቀነስ የልጅዎን እድገትና የትምህርት ሁኔታ ማሻሻል ነዉ፡፡የህክምና ባለሙያዎ በአካባቢዎ የሚገኙና ልጅዎን ሊረዱ/ሊያግዙ የሚችሉ አካላቶችን በማፈላለግ ሊያግዝዎ ይችላል፡፡ ሊደረጉ ከሚችሉ ህክምናዎች ዉስጥ፡-

 • የመግባባት ክህሎትና የባህሪ ለዉጥ ህክምናዎች፡-

  የልጁን ማህበራዊ፣ ቐንቐና የባህሪ ችግሮች ላይ የሚሰሩ ብዙ ፕሮግራሞች/መርሃግብሮች አሉ፡፡ የተወሰኑት ፕሮግራሞች የልጁን የሚያስቸግሩ ባህሪያቶችን ለመቀነስና አዳዲስ ችሎታዎችን ማስተማር ላይ ትኩረት ያደርጋሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ህፃናቱ በማህበራዊ ግንኙነታቸዉ ላይ እንዴት መሆን/ምን መተግበር   እንዳለባቸዉ ወይም ከሌሎች ሰዎች ጋር እንዴት መግባባት እንደሚችሉ ትኩረት ያደርጋል፡፡

 • ትምህርት፡-

  ኦቲዝም ያለባቸዉ ህፃናት በደንብ ለተቀረፃ የትምህርት መርሃግብር ጥሩ የሆነ አቀባበል አላቸዉ፡፡የተዋጣላቸዉ ፕሮግራሞች በዉስጣቸዉ ብዙ መርሃግብሮችን የሚይዙ ሲሆን ይህም የልጁን ማህበረዊ፣የመግባባት ክህሎትና ባህሪዉ ላይ ያተኮሩ ይሆናሉ፡፡

 • ቤተሰብ ተኮር ህክምና፡-

  ወላጆችና ሌሎች የቤተሰቡ አባላት የልጁን የመግባባት ክህሎት፣ችግሮችን የመፍታት ችሎታ ለማዳበር እንዲሁምበየቀኑ የሚጠቀምበትን የመግባባት ክህሎቱን ለማሳደግ በሚረዳዉ መልክ  እንዴት አብረዉ መጫወትና መግባባት እንደሚችሉ ማስተማር ያፈልጋል፡፡

 • መድሃኒት፡-

  ዋናዎቹን የህመም ምልክቶች የሚያሻሽል መድሃኒት እስከአሁን ባይገኝም ምልክቶቹን ለመቆጣጠር የሚረዱ የተወሰኑ መድሃኒቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ አንታይዲፕሬሳንትና አንታይሳይኮቲክ

Recent Posts

Comments

comments