አስም/Asthma

አስም/Asthma

 

አስም የአየር ቧንቧ እንዲጠብ፣አንዲያብጥና ተጨማሪ አክታ እንዲፈጥር የሚያደርግ የህመም አይነት ነዉ፡፡ ይህ የአየር ቧንቧ ጥበት ሂደት አተነፋፈስ ላይ ችግር እንዲፈጠር በማድረግ ሳል፣ ሲር ሲር የሚሉ ድምፆችና የትንፋሽ መቆራረጥ እንዲመጣ/እንዲከሰት ያደርጋል፡፡

የህመሙ ምልክቶች

 

የህመሙ ምልክቶች ከመጠነኛ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ሊድረስ የሚችል ሲሆን ከሰዉ ሰዉ ይለያያል፡፡ህመሙ አንዳንዴ ብቻ ሊከሰት ይችላል፡፡ሌሎች ላይ ደግሞ ሁል ጊዜ ሊሆን ይችላል፡፡የህመሙ ምልክቶች

• የትንፋሽ ማጠር
• ደረትን ወጥሮ መያዝ/የደረት ላይ ህመም
• በትንፋሽ ማጠር ምክንያት፣ በሳልና ሲር ሲር በሚል ምክንያት እንቅልፍ ማጣት
• ወደዉጪ በሚተነፍሱበት ወቅት ሲር ሲር የሚል ድምፅ መኖር
• ጉንፋን በሚይዝዎት ወቅት ሊባባስ የሚችል ሳል ወይም ሲርሲር የሚል ድምፅ መከሰት

 

የአስም ህመምዎ መባባሱን የሚያሳዩ ምልክቶች፡

 

• የአስም ህመም ምልክቶች ተደጋግሞ መከሰትና የሚያስጨንቅዎ ከሆነ
• የአተነፋፈስ ችግርዎ እየጨመረ መምጣት
• የአስም ህመምዎን በፍጥነት ሊያሻሽሉ የሚችሉ መድሃኒቶችን በተደጋጋሚ መዉሰድ ካለ

 

አስምን ሊያባብሱ የሚችሉ ነገሮች

 

• የአየር ዉስጥ አለርጂዎች፡- የአበባ ሽታ( ፖለን)፣ሻጋታ፣ የበረሮ ሽታ፣ አቧራ
• እንደ ጉንፋን ያሉ የመተንፈሻ አካል አንፌክሸኖች መኖር
• የአካል እነቅስቃሴ ካደረጉ በኃላ የሚመጣ
• ቀዝቃዛ አየር
• የአየር መበከል፤ለምሳሌ በጭስ
• መድሃኒቶች፡- ቤታ ብሎከርስ፣አስፕሪን፣አይቡፕሮፌን
• የስሜት መለዋወጥ፣ ጭንቀት
• የቃር ህመም
• በተወሰኑ ሴቶች ላይ በወር አበባ ዑደት ወቅት ሊባባስ ይችላል፡፡

ለአስም የሚያጋልጡ ነገሮች

አስም እንዲከሰት የሚደርጉ የተለያዩ ነገሮች አሉ፡፡እነዚህም
• በቤተሰብ ዉስጥ መሰል ችግር ካለ
• ሌሎች የአለርጂ ህመሞች ካለዎ(የቆዳ፣የሳይነስ)
• ክብደት መጨመር
• የሚያጨሱ ከሆነ
• ሌላ የሚያጨስ ሰዉ ካለ(የሲጋራ ጭስ መማግ)
• ለአየር ብክለት መጋለጥ
• እንደ እርሻ፣ የፀገር ስራና ከፋብሪካ ጋር የተገናኙ ኬሜካሎች ከስራቹ ሁኔታ የተነሳ የተጋለጡ ሰዎች
• ለአለርጂዎች፣ለተወሰኑ የበሽታ አምጪ ጀርሞች የተጋለጡ ሰዎችም ለህመሙ ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡

 

የህክምና ባለሙያዎን ማማከር የሚገባዎ መች ነዉ?

ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ አስም ለህይወት አስጊ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ የህመምዎ ምልክቶች እየተባባሱ ከመጡ የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ያስፈልጋል፡፡ የሚከተሉት ምልክቶች ካለዎ የህክምና ባለሙያዎን በፍጥነት ያማክሩ፡፡
• የትንፋሽ ማጠር ወይም ሲር ሲር የሚለዉ ድምጽ በፍጥነት ከተባባሰ
• እንደ አልቡቴሮል ያሉ ለድንገተኛ ጊዜ የሚሆኑ መድሃኒቶችን ወስደዉ የማይሻሻል ከሆነ
• መጠነኛ እንቅስቃሴ በሚያደርጉበት ወቅት የትንፋሽ ማጠር የሚከሰት ከሆነ

 

አስም እንዴት ሊመጣ ይችላል

ለምን የተወሰኑ ሰዎች አስም እንደሚያዙና ሌሎች ደግሞ ለምን እንደማይያዙ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ አስም የአካባቢያዊና ከዘር ጋር በተገናኘ ሊከሰት የሚችል የህመም አይነት ነዉ ተብሎ ይገመታል፡፡

 

የአስም ህክምና

አስም በህክምና ሊድን አይችልም፡፡ ነገር ግን የህመም ምልክቶቹን ልንቆጣጠራቸዉ እንችላለን፡፡ አስም በጊዜ ሂደት ብዙዉን ጊዜ ሊለዋወጥ ስለሚችል ከህክምና ባለሙያዎ ጋር በመመካከር መድሃኒትዎን እንደአስፈላጊነቱ ማስተካከል ያስፈልጋል፡፡

አስምን ሊያስነሱ የሚችሉ ነገሮችን መከላከል፡-አስምን ሊያስነሱ/ሊያባብሱ የሚችሉ ነገሮች መቀነስ አስምን ለመቆጣጠር ከሚረዱ መንገዶች አንዱ ነዉ፡፡ከነዚህም ዉስጥ

• ቅዝቃዜ በሚኖርበት ወቅት አፍና አፍንጫን መሸፈን
• ሻጋታን ማስወገድ፡- የሻጋታ ቡናኝን ለመከላከል በሻወር ቦታ፤በኩሽናና በመኖሪያ ቤትዎ አካባቢ ያሉ ሻጋታዎችን ማስወገድ
• ከቡናኝ መከላከል
• በመደበኛ ሁኔታ የመኖሪያ ቤትዎን ማፅዳት
• መደበኛ የሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ

Comments

comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *