የአባለዘር ህመምና ምልክቶቻቸዉ

የአባለዘር ህመምና ምልክቶቻቸዉ

የአባለዘር ህመም ማንኛዉም ከሰዉ ወደ ሰዉ በግብረስጋ ግንኙነት አማካይነት ሊተላለፍ የሚችል የህመም አይነት ነዉ፡፡ የአባለዘር ህመምን የሚያመጡ ከ30 በላይ የሆኑ የባክቴሪያ፣ የቫይረስና የፓራሳይት አይነቶች አሉ፡፡
እነዚህ ተዋህሲያን ሊያመጧቸዉ ከሚችሉዋቸዉ የህመም አይነቶች ዉስጥ በብዛት የሚታዩት ጨብጥ፣የክላሚዲያ ኢንፌክሽን፣ቂጥኝ፣ ትራኮሞኒያሲስ፣ ከርክር፣ የብልት ላይ ቁስለቶች(ሃርፐስ ጄኒታሊስ፣ የብልት ላይ ኪንታሮት)፣ የኤች አይ ቪ በሽታና የሄፓታይትስ ቢ(HBV) እንፌክሽን ናቸዉ፡፡
ከነዚህ ኢንፌክሽኖች ዉስጥ ኤችአይቪ፣ቂጥኝና ሄፓታይቲስ ቢ ከእናት ወደልጅ እንዲሁም በደምና የተበከሉ ነገሮች ሊተላለፉ ይችላሉ፡፡

የአባለዘር ህመም ምልክቶች

የአባላዘር ህመም ምልክቶች ሁሌም ላይታዩ ይችላሉ፡፡ እርስዎ የአባለዘር ህመም ምልክቶች አሉኝ ብለዉ ካሰቡ ወይም ለአባለዘር ህመም ተጋልጠዉ ከነበረ የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ይጠበቅብዎታል፡፡ አንዳንዱ የአባለዘር ህመሞች በቀላሉ የሚታከሙ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ውስብስብ ናቸዉ፡፡
ብዙዉን ጊዜ የአባለዘር ህመሞች ምንም አይነት የህመም ምልክቶች አያሳዩም፡፡ ምንም አይነት ምልክቶች ባይኖሩም/ባይታዩም ህመሙ ከአንዱ ሰዉ ወደ ሌላዉ ሰዉ ሊተላለፍ ይችላል፡፡ ስለሆነም በግብረስጋ ግንዘኙነት ወቅት ኮንደም እንዲጠቀሙ ይመከራሉ፡፡

ክላሚዲያ

ክላሚዲያ የባክቴሪያል እንፌክሽን ሲሆን ሊያሳያቸዉ ከሚችላቸዉ ምልክቶች ዉስጥ
• ሽንት በሚሸኑበት ወቅት ህመም መኖር
• የታችኛዉ የሆድ ክፍል ላይ ህመም መኖር
• በወንዶችም ይሁን ሴቶች ላይ የብልት ፈሳሽ መታየት
• በሴቶች ላይ በግብረስጋ ግንኙነት ወቅት ህመም መኖር/መከሰት
• በወር አበባ ዑዳት መሃል ከብልት ደም መኖር
• በወንዶች ላይ የዘር ፍሬ ላይ ህመም ናቸዉ
የጨብጥ የህመም ምልክቶች
ጨብጥ በባክቴሪያ ምክንት የሚመጣ ሲሆን ከብልት ዉጪ በአፍ ዉስጥ፣ጉሮሮ፣ፊንጥጣ እና አይን ላይ ሊታይ ይችላል፡፡የህመሙ ምልክቶች እንፌክሽኑ ከመጣ በ10 ቀናት ዉስጥ ሊታይ ይችላል፡፡

የህመሙ ምልክቶች

• ወፈር ያለ መግል ወይም ደም የቀላቀለ ከወንድ ወይም ሴት የብልት መታየት
• ሽንት በሚሸኑበት ወቅት የማቃጠል ስሜት
• ሴቶች ላይ የወር አበባ መብዛት ወይም በወር አበባ መሃል መድማት መኖር
• በወንዶች ላይ ህመም ያለዉ የወንድ ዘር ፍሬ እብጠት
• ሰገራ ሲቀመጡ ህመም መኖር ናቸዉ፡፡
ይቀጥላል

Comments

comments