የሰዉነት ሸንተረር (Stretch marks)

የሰዉነት ሸንተረር (Stretch marks)

ሸንተረር ቀይ፣ሃምራዊ ወይም የወይንጠጅ ቀለም ያለዉና በብዛት በሆድ፣ ጡት፣በክርና ትከሻ መሃል፣በመቀመጫና በታፋ ላይ የሚከሰት ሲሆን በሂደት መልኩ እየደበዘዘ ወደ ነጭ ወይም ግራጫ መልክ እየተቀየረ የሚመጣ የቆዳ ላይ ችግር ነዉ፡፡

ምልክቶች

ሁሉም ሸንተረሮች አንድ አይነት አይደሉም፡፡ የመለያየታቸዉ ምክንያት ደግሞ በሰዉነት ላይ ከወጡ በኃላ የነበራቸዉ እርዝማኔ፣ ሸንተረሩ እንዲከሰት እንደአደረገዉ ምክንያትና የተከሰተ ቦታ እንዲሁም የቆዳዎ ሁኔታ ናቸዉ፡፡

· በቆዳዎ ላይ ወደ ዉስጥ ገባ ያለ መስመር

· ቀይ፣ሃምራዊ ወይም የወይንጠጅ ቀለም ያላቸዉ ሸንተረሮች በብዛት መከሰት

· ቀስ በቀስ እየደበዘዘ ወደ ነጭ ወይም ግራጫ መልክ የሚቀየር ደማቅ የሆነ ሸንተረር መከሰት ናቸዉ፡፡

ለሸንተረር መከሰት ምክንያቶች

ሸንተረር የሚከሰተዉ የሰዉነት ቆዳ በሚወጠርበት ጊዜ ሲሆን ይህ እንዲፈጠር የሚያደርጉ ብዙ ነገሮች አሉ:: እነርሱም

· እርግዝና

· ክብደት መጨመር

· መድሃኒቶች፡- የኮርቲኮስቴሮይድ ክሬም፣ ሎሽን ወይም እንክበሎች

· ህመሞች፡- የአድሬናል ግላንድ/ዕጢ ችግሮችና ኩሽንግ ሲንድረም የሚባለዉ ህመም ሲኖር የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡

ተጋላጭነትዎን የሚጨምሩ ነገሮች

ምንም እንኳን ሸንተረር በማንኛዉም ሰዉ ላይ ሊከሰት የሚችል ቢሆንም ይበልጥ የመከሰቱን ነገር ሊጨምሩ የሚችሉ ሁኔታዎች

· ሴት መሆን

· በቤተሰብ ዉስጥ መሰል ችግር መኖር

· እርግዝና ከነበረ

· ከመጠን ያለፈ ክብደት ወይም ዉፍረት መኖር

· ክብደት በፍጥነት የሚጨምሩ ወይም የሚቀንሱ ሰዎች- ለምሳሌ በእርግዝና ጊዜያት

· ኮርቲኮስቴሮይድ መድሃኒት የሚወስዱ ሰዎች

ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች፡- የሚሰጡት ህክምናዎች ሸንተረሩ እንዲደበዝዝ ቢደርግም ሙሉ በሙሉ ሊያጠፋዉ ግን አይችልም፡፡ ምንም እንኳ ሸንተረር ሲከሰት ሰዎች ላይ አሳሳቢ ቢመስልም/ cosmetic concern ቢኖረዉም/ በጤናዎ ላይ ምንም ጉዳት አያደርስም፡፡ በጊዜ ሂደት ቀስ በቀስ እየደበዘዘ ይመጣል፡፡

ሊደረጉ ከሚችሉ ህክምናዎች ዉስጥ

· የሌዘር ህክምና፡- ይህ የህክምና ዘዴ በቆዳዎ ዉስጥ ያሉትን ኮላጂን፤ኢላስቲን ወይም ሜላሊን የተባሉ ኬሚካሎችን እንዲመረቱ በማነቃቃት ችግሩ እንዲሻሻል ያደርጋል፡፡

· የቤት ዉስጥ ህክምናና የአኗኗር ዘይቤ ለዉጥ፡- እንደ ክሬም፣ ቅባትና ሌሎች ዉጤቶች ሸንተረርን ለመቀነስ ይረዳሉ ተብሎ ይታሰባል፡፡ እነዚህ ነገሮች በዉስጣቸዉ የኮኮአ ቅቤ፣ቫይታሚን ኢ ወይም ግላይኮሊክ አሲድ ስላላቸዉ ብዙ ባይረዱም በመጠቀምዎ የሚኖራቸዉ ጉዳት ስለሌለ መጠቀም ይችላሉ፡፤

እንዴት መከላከል ይቻላል

የቱንም ያህል መጠን ያለዉ ሎሽንም ይሁን ቅባት በሰዉነትዎ ላይ ቢቀቡ ሸንተረርን መከላከል አይችሉምም፡፡ ጤናማ ክብደትን መጠበቅ የሸንተረርን የመከሰት ሂደት ለመቀነስ ከሚረዱ መንገዶች ዋነኛዉ ነዉ፡፡

Comments

comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *