መጥፎ የእግር ጠረን

መጥፎ የእግር ጠረን

በአብዛኛዉ ጊዜ መጥፎ የእግር ሽታ የሚያመጡ ነገሮች በቀላሉ ሊታከሙ/ሊወገዱ የሚችሉ ናቸዉ፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች ላይ የእግር ሽታዉ በቀላሉ የማይጠፋና ለረጅም ጊዜ ሊቆይ ስለሚችል የህክምና ባለሙያ እርዳታ ያስፈልጋል፡፡ የህክምና ባለሙያዉ የሽታዉን መንስኤ ካረጋገጠ በኃላ አስፈላጊዉን ህክምና እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡

መጥፎ የእግር ጠረን መንስኤዎች

ባክቴሪያ:-

ከ10 እስከ 15 በመቶ የሚደርሱ መጥፎ የእግር ሽታ እንዲከሰት የሚያደርጉት በስኒከር መጫሚያዎች ዉስጥ የሚገኙ ባክቴሪያዎች ናቸዉ፡፡ ባክቴሪያዎቹ የሞቱ የቆዳ ሴሎችን የሚመገቡ ሲሆን እርጥበታማና ላብ እንዲከሰት የሚያደርጉ የእግር ጫማዎች ባክቴሪያዎቹን የመሳብና ምቹ መራቢያ ቦታዎች ይፈጥርላቸዋል፡፡

እነዚህ ባክቴሪያዎች ኦርጋኒክ አሲድና ሰልፈር ዉሁድ ስለሚያመርቱ እግር የተበላሸ እንቁላል ጠረን እንዲኖረዉ  ያደርጋሉ፡፡

ፈንገስ እንፌክሽን፡-

መጥፎ የእገር  ሽታ በብዛት ከሚያመጡ መንስኤዎች ዉስጥ አንዱ የሆነዉ የፈንገስ እንፌክሽን ሲሆን ፈንገስ በተጨማሪም በእግር መርገጫ/ተረከዝ ቆዳ ላይ የመድረቅና በእግር ጣቶች መሃል የቆዳ መላላጥ እንዲመጣም ያደርጋል፡፡ይህ አትሌትስ ፉት ወይም ቲንያ ፔዲስ ይባላል፡፡ ቲንያ ፔዲስ ከሰዉ ወደ ሰዉ የሚተላለፍ ሲሆን በእርጥበት አዘል አካባቢዎች ለምሳሌ የልብስ መቀየሪያ ስፍራዎች( ፈንገሱ ሌላ ያለተሸፈነ ሰዉ ቆዳ ጋር የሚገናኝበት ስፍራ) ፈንገሱ በብዛት ሊገኝ ስለሚችል መተላለፉን ሊጨምር ይችላል፡፡

የተሰነጣጠቀ የእግር ቆዳ ለፈንገሱ በቀላሉ መያዝ ምቹ እድል ሊፈጥር ይችላል፡፡

ከመጠን በላይ ላብ( Hyperhidrosis)

የላብ እጢዎች ከመጠን ያለፈ ላብ የሚያመርቱ ከሆነ መጥፎ ጠረን እንዲከሰት ምቹ ሁኔታን ሊፈጥር ይችላል፡፡ አንዳንድ ሰዎች በብብታቸዉና በእግር/እጅ መዳፍ ዉስጥ ከመጠን ያለፈ ላብ ሊያልባቸዉ ይችላል፡፡  ይህ ከመጠን ያለፈ ላብ መጥፎ የብብትና እግር ጠረን እንዲከሰት ሊያደርግ ይችላል፡፡ እነዳንድ ሰዎች ላይ ይህ ከመጠን ያለፈ ላብ የመሸማቀቅ ወይም የማፈር ስሜት ሊፈጥርባቸዉ ስለሚችል እራሳቸዉን ከማህበራዊ መስተጋብር ሊያገሉ ይችላሉ፡፡

ሊደረግ የሚችል ሕክምና

የእግርን ንፅህና በአግባቡ በጠበቅ ባክቴሪያዉን ማጥፋት ይቻላል፡፡ እግርን በየቀኑ በመታጠብ፣የእግር ካልሲዎችን/ሹራቦችን ቶሎ ቶሎ በመቀየርና እንዲሁም ጫማን በመቀያየር የእግር ላይ ባክቴሪያ እድገትን መቀነስ ይቻላል፡፡

የችግሩ መንሳኤ ፈንገስ ከሆነ ፓውደር ወይም መድሃኒቶችን በመጠቀም ሊታከም ይችላል።

ለተወሰኑ ጉዳዩች የቆዳ ህክምና ባለሙያዎች መዳኒቶችን ሊያዙ ይችላሉ።

Comments

comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *